NEWS

Happy Easter

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች፤ እንኳን ለፋሲካ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡

ኩባንያችን ጥቁር ዓባይ ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ኃላ/የተ/የግ/ ማህበር በንጋት ኮርፖሬት ስር ከሚገኙ ኩባንያዎች መካከል አንዱ ሲሆን፤ በኮምቦልቻ፣ አዳማ እና ጅቡቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችን፣ በባህር ዳር እና ሚሌ ማስተባባሪያ ጽ/ቤቶችን፣ በጎንደር እና ደብረ ብርሃን ኦፕሬሽን ማዕከላትን እንዲሁም በወረታ፣ ኮምቦልቻ፣ ጎንደር፣ ሞጆ፣ ቦሌ አየር መንገድ፣ ቃሊቲ እና አዳማ የጉምሩክ እና የትራንዚት ሎጂስቲክስ ማዕከላትን በማደራጀት ስራውን እያሳለጠ ይገኛል፡፡
ኩባንያችን በሀገራችን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ዘርፍ ውስጥ ካሉት መሪ ኩባንያዎች ውስጥ አንዱ ለመሆን በቅቷል። የኩባንያው በኮምቦልቻ፣በሞጆ ህንጻዎች እና በጎንደር መጋዘን ያለው ሲሆን፤ በአዲስ አበባ 2B+G+14 ሁለገብ ህንጻ እና በኮምቦልቻ G+10 ሁለገብ ህንጻ በግንባታ ላይ ይገኛሉ። አሁን ላይ ኩባንያው በውድድር አልፎ በመንግስት ተመርጠው እውቅናና ንግድ ፈቃድ ከተሰጣቸው አዳዲስ የመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት ኦፕሬተሮች ውስጥ አንዱ ሲሆን በዚህ ዘርፍ አለም ዓቀፍ ገበያውን እየተቀላቀለ ይገኛል።
ኩባንያው በርካታ አገልግሎቶችን የሚሰጥ ሲሆን፤ ከነዚህ ውስጥ ዋና ዋናዎቹ፤
• ደረቅ ጭነት ትራንስፖርት (ኢምፖርት፣ ኤክስፖርት እና የሀገር ውስጥ ጭነት) ፣
• የአሽከርካሪ እና ባለሙያዎች ስልጠና አገልግሎት፣
• የተሽከርካሪ ምርመራ አገልግሎት፣
• የአነስተኛ ተሽከርካሪ ጥገና አገልግሎት፣
• መለዋወጫ እና የጎማ አስመጪነት ንግድ አገልግሎት፣
• የጭነት አስተላላፊ አገልግሎት፣
• የጉምሩክ ክሊራንስ አገልግሎት፣
• የህንፃና ማሽነሪ ኪራይ አገልግሎት ናቸው፡፡
ውድ የኩባንያችን ሰራተኞች ኩባንያችን ለዚህ ደረጃ የደረሰው በሁላችንም የተባበረ ጥረት ስለሆነ፤ ቀጣይም ከዚህ በበለጠ እንድንበረታ እያልን፤ እንኳን ለፋሲካ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ለማለት እንወዳለን፡፡

All Posts

Latest News

Eid

Categories

Best Multimodal Service

Support Email

info@tikurabaytl.com

Phone Support

+2519-11-24-42-38

Location

Addis Ababa: Bole Gazebo Adebabay Sterling Building 3rd Floor

© 2025 Tikurabay Transport & logistics 1992-2025
Scroll to Top