Latest News

BLOG POSTS

News & Announcements

News

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች፤ እንኳን ለኢድ በሰላም አደረሳችሁ፡፡

ኩባንያችን ጥቁር ዓባይ ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ኃላ/የተ/የግ/ ማህበር በንጋት ኮርፖሬት ስር ከሚገኙ ኩባንያዎች መካከል አንዱ ሲሆን፤ በኮምቦልቻ፣ አዳማ እና ጅቡቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችን፣ በባህር ዳር እና ሚሌ ማስተባባሪያ ጽ/ቤቶችን፣ በጎንደር እና ደብረ ብርሃን ኦፕሬሽን ማዕከላትን እንዲሁም በወረታ፣ ኮምቦልቻ፣ ጎንደር፣ ሞጆ፣ ቦሌ አየር መንገድ፣ ቃሊቲ እና አዳማ የጉምሩክ እና የትራንዚት ሎጂስቲክስ ማዕከላትን በማደራጀት ስራውን እያሳለጠ ይገኛል፡፡
ኩባንያችን በሀገራችን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ዘርፍ ውስጥ ካሉት መሪ ኩባንያዎች ውስጥ አንዱ ለመሆን በቅቷል። የኩባንያው በኮምቦልቻ፣በሞጆ ህንጻዎች እና በጎንደር መጋዘን ያለው ሲሆን፤ በአዲስ አበባ 2B+G+14 ሁለገብ ህንጻ እና በኮምቦልቻ G+10 ሁለገብ ህንጻ በግንባታ ላይ ይገኛሉ። አሁን ላይ ኩባንያው በውድድር አልፎ በመንግስት ተመርጠው እውቅናና ንግድ ፈቃድ ከተሰጣቸው አዳዲስ የመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት ኦፕሬተሮች ውስጥ አንዱ ሲሆን በዚህ ዘርፍ አለም ዓቀፍ ገበያውን እየተቀላቀለ ይገኛል።
ኩባንያው በርካታ አገልግሎቶችን የሚሰጥ ሲሆን፤ ከነዚህ ውስጥ ዋና ዋናዎቹ፤
• ደረቅ ጭነት ትራንስፖርት (ኢምፖርት፣ ኤክስፖርት እና የሀገር ውስጥ ጭነት) ፣
• የአሽከርካሪ እና ባለሙያዎች ስልጠና አገልግሎት፣
• የተሽከርካሪ ምርመራ አገልግሎት፣
• የአነስተኛ ተሽከርካሪ ጥገና አገልግሎት፣
• መለዋወጫ እና የጎማ አስመጪነት ንግድ አገልግሎት፣
• የጭነት አስተላላፊ አገልግሎት፣
• የጉምሩክ ክሊራንስ አገልግሎት፣
• የህንፃና ማሽነሪ ኪራይ አገልግሎት ናቸው፡፡

All Posts

Latest News

Categories

Best Multimodal Service

Scroll to Top